ወደ እስልምና ሀይማኖት ገብተህ ሙስልም ለመሆን ድምጽህን በማሰማት መናገር ያስፈልገሃል።የተናገርከውን ትርጉሙን ማወቅና ማመን ያስፈልገሃል።
እነዚህ በዐረብኛ የሆኑ ቃላቶች ናቸው፤ ሸሃዳ ይባላል። (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ትርጉሙ /ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ማለት ነው/። ( ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ። የማሪያም ልጅ ዒሳ የአላህ ባሪያና መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ)
አሁን በዐረብኛ ቋንቋ በል:
አሽሀዱ አልላ ኢላሀ ኢለላሁ፤ ወአሽሀዱ አንነ ሙሀመደን ረሱሉላህ፤
ወአሽሀዱ አንነ ዒሰብኑ መርየመ ዐብዱላሂ ወረሱሉሁ።